በውይይት መድረኩ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት በአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በህዝብ ግንኙነት እና ሚዲያ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ስዩም ከበደ እንደገለፁት ዘመነ መረብን የሚመጥን ጠንካራ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ሥራ በመስራት ከጉባኤ እስከ ጉባኤ ያስመዘገብናቸው ሁሉም ድሎች የተገኙት ሕዝቡ በፓርቲያችን ላይ ባሳደረው እምነት፣ በሰጠው ድጋፍና ባደረገው ተሳትፎ ልክ በመሆኑ እስከ ቀጣዩ ጉባኤው ድረስም ሕዝቡን በሁሉም ሀገራዊና ከባቢያዊ አጀንዳዎች ዙሪያ በንቃትና በስፋት በማሳተፍ በልዩ ትኩረትና በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።