በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የመስቀልና የኢሬቻ በዓላትን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ምርቶች የሚቀርቡበት ደማቅ ባዛር ተከፈተ።

user 24-Sep-2025 ወቅታዊ ጉዳይ

በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የመስቀልና የኢሬቻ በዓላትን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ምርቶች የሚቀርቡበት ደማቅ ባዛር ተከፈተ።

የክፍለ ከተማው ንግድ ጽ/ቤት የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላትን ምክንያት በማድረግ "በእምርታ እና ማንሰራራት ለህዝባዊ በዓላት" በሚል መሪ ቃል ደማቅ ባዛር በክፍለ ከተማው ፊት ለፊት ማካሄድ ጀመሯል ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት ኤግዚብሽንና ባዛሮች የኑሮ ውድነትን ከማረጋጋት አኳያ የላቀ ሚና እንደሚጫወቱ ገልጸው አምራቾችን በማበረታታት ህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ መሸመት እንዳለበት ተናግረዋል።

በባዛሩ የተለያዩ የሰብል ፣ የአትክልትና የኢንዱስትሪ ምርቶች በስፋት ፣ በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረቡበት መሆኑን ጠቅሰው ይህም በዓላትን ምክንያት በማድረግ ያለ አግባብ የሚፈጠር የዋጋ ጭማሪንና የምርት አቅርቦት እጥረትን የሚከላከል መሆኑን ገልፀው የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች በባዛሮቹ በመገኘት እንዲገበያዩ ጥሪ አቅርበዋል ።

የክፍለ ከተማው ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሃንስ ነጋሽ በበኩላቸው በኤግዚቢሽንና ባዛሩ አምራቹና ሸማቹን የሚያገናኝ ከመሆኑም ባሻገር ሀገር በቀል ምርቶችን የሚያገኙበት ስለሆነ የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች የህዝባዊ የበዓላት ዝግጀት የሚሆኑ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ወደ በሚቀርበው አካባቢ በመሄድ ምርቶቹን እንዲሸምቱ ጠቁመዋል፡፡

Related Post

ልዩ ዜና