#ጳጉሜ_4_የማንሰራራት_ቀን

user 09-Sep-2025 ማህበራዊ ጉዳዮች

#ጳጉሜ_4_የማንሰራራት_ቀን

በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜ 4 የማንሰራራት ቀንን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ6 ኪሎ _በሽሮ ሜዳ _እንጦጦ የለማው የኮሪደር ልማትና ሸገር የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶችን ጉብኝት ተካሄደ።

በክፍለ ከተማው " ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት !! " በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘው የማንሰራራት ቀን ምክንያት በማድረግ የኮሪደር ልማት ስራዎች ተጎብኝተዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው እንደተናገሩት ባለፉት ዓመታት መንግስት በርካታ ሰው ተኮር የሆኑ ተግባራትን ፣ የማይደፈሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ፣ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ፣ የኮሪደር ልማትና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን በማከናወን ከቁልቁለት ጉዞ አውጥቶ የማንሰራራት ጊዜያት ላይ ደርሰናል መጪዎች ጊዜያት የከፍታ ዘመን እንዲሆን ሁላችንም በተሰማራንበት ዘርፍ የላቀ ለውጥ የምንተጋበት መሆን ይገባል ብለዋል።

የኮሪደር ልማቱ የአስፓልት መንገድ ዝርጋታ ፣የእግረኛ መንገድ ፣ የሳይክል መስመር ፣ የህጻናት መጫወቻ ቦታዎች ፣ የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራዎች ፣ የህዝብ መዝናኛ ፕላዛዎችና አረንጓዴ ፓርኮች ፣ መጸዳጃ ቤቶች ፣ የንግድ ሱቆች ፣ የመኪና ማቆሚያና ተርሚናሎች በውስጡ አካቷል።

Related Post

ልዩ ዜና