የጉለሌ ክፍለ ከተማ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ለ2017 /18 ዓ.ም በክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሚተከሉ 1.5 ሚሊዮን ችግኞች ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

user 23-Jun-2025 ፖለቲካ

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ለ2017 /18 ዓ.ም በክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሚተከሉ 1.5 ሚሊዮን ችግኞች ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

የክፍለ ከተማው ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ለ2017/18 ዓ.ም ለአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሚተከሉ ችግኞች ዝግጅት በእንጦጦ ችግኝ ጣቢያ እያደረገ ይገኛል፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ኤደን ካሳ እንደተናገሩት በክፍለ ከተማችን በክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ለተለያዩ ጥቅም የሚሰጡ ችግኞች በእንጦጦ ችግኝ ማፈያ ጣቢያ ችግኞቹ ለመትከል ዝግጁ መሆናቸውን እና ችግኙች የተፈሉበትን አግባብ የእንክብካቤ ስራውን በችግኝ ጣቢያው ከሚሰሩ ሰራተኞች ልምድ መውሰዳቸው በቀጣይ ለአረንጓዴ አሻራ እንደሚጠቅማቸው ተናግረዋል፡፡

በእንጦጦ ችግኝ ማፈያ ጣቢያ በራሱ በክፍለ ከተማው አቅም የችግኝ ማፍላት ተግባር መከናወኑ ከዚህ በፊት ይወጣ የነበረውን የችግኝ ግዢ ማስቀረት መቻሉን ሃላፊዋ ተናግረዋል፡፡

በእንጦጦ ችግኝ ጣቢያ ለ2017 /18 ዓ.ም ለአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሚውሉ የጥላ ዛፎች ፣ የጤና ጥቅም ፣ቅማማ ቅመሞች ፣ የውበት ዛፎች ፣ የቡናና ፍራፍሬ ችግኞች እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

Related Post

ልዩ ዜና