የኮሪደር ልማት ባጭር ቀናት እንዲጠናቀቅ የድጋፍና ክትትል ምልከታው ተጠናክሮ ቀጥሏል።

user 02-Jun-2025 ልማት

የኮሪደር ልማት ባጭር ቀናት እንዲጠናቀቅ የድጋፍና ክትትል ምልከታው ተጠናክሮ ቀጥሏል።

************************

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊና የኮሪደር ልማት ዋና አስተባባሪ ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው ከ4ኪሎ ሽሮ ሜዳ ቁስቋም እንጦጦ ማርያም በራጉኤል ቤተክርስቲያን ዞሮ ቦታኒክ ጋርደን የሚዘልቀው 2ኛው ዙር የጉለሌ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት እድገት ለማፋጠንና ለህብረተሰቡ የሚሰጡ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ስራዎችን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ በጥሩ ተነሳሽነት ተሰርቶ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ በመስክ ጉብኝታቸው ተመልክተዋል።

በምልከታው ላይም የከተማ የኮሪደር ደጋፊ አመራሮች እና የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ይከበር ስማቸው እና የጉለሌ ክ/ከ ወረዳ 3 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ በሐይሉ እምወድ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ተዘዋውረው ምልከታ በማድረግ በከተማ እና በክፍለ ከተማ አመራሮች ፕሮጀክቱን ባጭር ቀናት ለማጠናቀቅ አስፈላጊው የድጋፍና ክትትል ቁጥጥር ተደርጓል።

Related Post

ልዩ ዜና