"የአገልግሎት ቀንን ለተገልጋይ ብቻ !! "

user 03-Sep-2025 ማህበራዊ ጉዳዮች

"የአገልግሎት ቀንን ለተገልጋይ ብቻ !! "

አስተዳደሩ የአገልግሎት ቀንን ለተገልጋይ ብቻ የሚለውን አቋም ይዞ በአንድ ማዕከል ህዝቡን በግልፅነት ማገልገል ከጀመረ ሰነባብቷል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የአንድ ማዕከል አገልግሎት ረቡዕና ዓርብን ማዕከል አድርጎ ከክፍለ ከተማ ባሉ በሁሉም ጽህፈት ቤቶች እየተሰጠ ሲሆን ለተገልጋይ ክብር ሲባል የደንበኛ መረጃ መስጫ ማዕከላትንም ማደራጀት ተችሏል። በዚህም በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እየተፈቱ ይገኛል።

በዛሬው ዕለትም በሁሉም ጽ/ቤቶች የተገልገይን ዕለት ለተገልጋይ ብቻ በማዋል ተገልጋዩን ህብረተሰብ በክብር ፣ በቅንነት በታማኝነትና ውጤታማ በሆነ አሰራር እያገለገለ ውሏል።

በአገልግሎት አሰጣጡ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ ፣ የክፍለ ከተማ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አንድ ዓይነት ጉዳይ ያላቸውን በጋራ ምላሽ በመስጠት፣ ወረፋን በመጠበቅ የሚጠፋ ጊዜን በመቆጠብ፣ ብልሹ አሰራርን ለማስወገድና ግልፀኝነትን በመፍጠር በልዩ ትኩረት እየተሠራ ነው።

Related Post

ልዩ ዜና