በአንድነቷ የጠነከረች ብሩህ ኢትዮጵያ !! "
በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የገዢ ትርክት ማስረጽ ዓላማ ያደረገ " በአንድነቷ የጠነከረች ብሩህ ኢትዮጵያ !! " በሚል መሪ ቃል የኪነ ጥበብ ምሽት ተካሄደ ።
በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ዋቅጋሪ ባስተላለፉት መልዕክት ሀገራዊ ገዢ ትርክቶችን በኪነ ጥበብ በመግለጽ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ለማጉላት አይነተኛ አስተዋጽዖ አለው ያሉ ሲሆን ሁሉም የማህብረሰብ ክፍል ብሔራዊነትን የሚያጎላ ሊያግባቡ የሚችሉ የወል ገዢ ትርክትን በማስረጽ የኢትዮጵያዊያ መጻኢ የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ በጋራና በአንድነት መስራት ይኖርብናል ብለዋል።
ኃላፊዋ አክለውም በክፍለ ከተማችን ገዢ ትርክቶችን በኪነ ጥበብ ስራዎች በማላቅ የተራራቁ አስተሳሰቦችን በማቀራረብ ነዋሪው አንድነቱን እንዲያጠናክር በማድረግ በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ማድረግ ይገባል ብለዋል።
የክፍለ ከተማው ባህል ፣ ኪነ ጥበብ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ባንቺ ጸሐይ በበኩላቸው በ2018 በጀት ዓመት ለ2ኛው ዙር የተዘጋጀ የገዢ ትርክት የማስረጽ መርሃ ግብር መሆኑን በመግለጽ የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ የጋራ የብሔራዊነት ትርክትን ማስረጽ ኪነ ጥበብ ድርሻዋ የላቀ ነው በመሆኑም የተለያዩ መድረኮችን በመፍጠር የህብረተሰባችንን ግንዛቤ ለማስፋት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍቅር ቶቤ በበኩላቸው በወረዳው ገዢ ትርክቶችን ለማስረጽ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸው የኪነ ጥበብ ምሽቶች በተለያዩ ጊዜያት እየተዘጋጁ የህብረተሰቡን ግንዛቤውን በማስፋትና የወል ትርክትን እየገነባን አብሮነትን በማጽናት በእህትማማችነትና በወንድማማችነት መርህ ላይ ቆመን ብልጽግናችንን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።
በኪነ ጥበብ ምሽቱ ላይ የህጻናት ህብረ ዝማሬ ፣ ሰርከስ ትርዒቶች ፣ ጭውውቶችና ድራማዎች ቀርበውበታል።