በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የአዲሱ ገበያ ክላስተር የአንድ ማዕከል ህዝባዊ የሰላም ሰራዊት ስምሪት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

user 24-Sep-2025 ወቅታዊ ጉዳይ

በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የአዲሱ ገበያ ክላስተር የአንድ ማዕከል ህዝባዊ የሰላም ሰራዊት ስምሪት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የአዲሱ ገበያ የአንድ ማዕከል የሰላም ሰራዊት ስምሪት የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ፣ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ ፣ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ ፣ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ጎዴቦ ፣ የከተማ ደጋፊ አመራሮች ፣ የፖሊስ አመራሮች ሌሎች የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት የአንድ ማዕከል ህዝባዊ የሰላም ሰራዊት ስምሪት ተሰጠ።

በመርሃ ግብሩ ላይ ስምሪት የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ፣ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ በመልዕክታቸው የሰላም ሰራዊቱ ከፀጥታ ሀይሉና ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት የአከባቢውን ሰላምና ደህንነት በንቃት እየጠበቀ ያለበት ሁኔታ አበረታች መሆኑን ገልፀው ስምሪት ወስዶ አከባቢን መጠበቅ የሰላም ሰራዊት የዘወትር ተግባር በመሆኑ በበዓላት ወቅት በልዩ ትኩረት አከባቢን የመጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ በበኩላቸው ሀይማኖታዊ እና ህዝባዊ የአደባባይ በዓላት በሚከበርበት ወቅት የህብረተሰቡን ሰላም ለማደፍረስ አጋጣሚውን የሚጠቀሙ ሀይሎች በመኖራቸው ህዝባዊ የሰላም ሰራዊቱ አካባቢውን የፀጥታ ችግሮች እንዳይከሰቱ መስራት ይገባል ብለዋል።

አቶ ሰለሞን አክለውም ህዝባዊ የሰላም ሰራዊት አባላትም የአካባቢያቸውን ሰላምና ፀጥታ አንዳች ችግር እንዳይከሰት ማንኛውንም ችግሮች ተጋፍጠው ስምሪታቸውን እንደሚያጠናክሩ ገልጸው በየደረጃው ያሉ የወረዳው የፓሊስ ሰራዊት አባላት፣የሰላም ሰራዊት ፣የቅጥር ጥበቃ እና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች የምስጋና እና የማበረታቻ መልእክት አስተላልፈዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አራጌ እሸቴ በበኩላቸው የመስቀል ደመራ እና ኢሬቻ በዓላት በሚከበርበት ወቅት በርካታ ህዝብ የሚሰባሰብባቸው እንደመሆኑ መጠን በሰላም ተከብረው እንዲጠናቀቁ ከብሎክ ጀምሮ የምንሰራው የፀጥታ ስራ እጅግ ወሳኝነት አለው የአንድ ማዕከል ህዝባዊ የሰላም ሰራዊት ስምሪት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚ

Related Post

ልዩ ዜና