የህብረተሰባችንን አገልግሎት ፍላጎት ለማርካት በትጋት እንሰራለን !!
በጉለሌ ክፍለ ከተማ የሴክተር ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ምልከታ ተደርጓል።
የባለጉዳይ ቀን አገልግሎት አሰጣጡን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ ፣የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ እንዲሁም የተቋማት ኃላፊዎች ተወካዮች የተገልጋዩችን ጥያቄያቸውን እየተቀበሉ ምላሽ እየሰጡ ይገኛል ።
በክፍለ ከተማው አገልግሎት በሚሰጥባቸው ተቋማት ኃላፊዎች ባሉበት ምልከታ የተደረገ ሲሆን በሴክተሮች ላይ ለተገልጋዮች ምላሽና ማብራሪያዎች ሲሰጡ ተመልክተናል።
በምልከታው በአመራሮችና እና በባለሙያዎች የባለ ጉዳይ አያያዝና አቀባበል እንዲሁም የተቀላጠፈ አገልግሎት ከመስጠት አንፃር መሻሻሎች መኖራቸውን ታዝበናል።
የባለ ጉዳይ ቀንን ለተገልጋዮች ብቻ በማዋል የህብረተሰቡን የመልካም አሰተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች በመፍታት እርካታ መጨመር ያስፈልጋል።