አስተዳደሩ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ ትውፊቱን ጠብቆ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

user 01-Oct-2025 ወቅታዊ ጉዳይ

አስተዳደሩ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ ትውፊቱን ጠብቆ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

(ጉለሌ ኮሙኒኬሽን ፣ 21 -01 -2018 ዓ.ም)

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ያሉበትን ደረጃ የከተማ ደጋፊ አመራሮች ፣ የክፍለ ከተማ አጠቃላይ አመራርና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት ገምግሟል።

በግምገማ መድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ፣ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ እንደተናገሩት የኢሬቻ በዓል የህብረ ብሔራዊ አንድነታችን መገለጫ በመሆኑ በዓሉ በሰላም እንዲከበሩ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ከአጎራባች የሸገር ክፍለ ከተማዎች ጋር ውይይቶች መካሄዳቸው ፣ የፓርቲውን አባላት ከብሎክ ጀምሮ ስምሪት መስጠት መቻሉ ፣ የሰላም ሰራዊት የቅጥር ጥበቃና የፀጥታ ተቋማትን በቅንጅት ወደ ስራ ማስገባት መቻሉ ፣የስጋት ቦታዎችን በመለየት የድንገተኛ እና አደጋሰ ስጋት ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሌሎች በርካታ ስራዎች መሰራታቸው ተገልጿል ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በበኩላቸው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በጥሩ ሁኔታ እየተመሩ እንደሚገኝ ጠቅሰው ተግባራትን ቀጣይነት ባለው መልኩ መምራት ፣ በቂ የሎጀስቲክ አቅርቦት ማዘጋጀት ፣ የአዲስ አበባ ህዝብ እንግዳ ተቀባይነቱን ማረጋገጥ ፣ ሁሉንም አደረጃጀት በመጠቀም ጠንካራ ስምሪት መስጠት ፣ ፈጣን የመረጃ ልውውጥ በመፍጠር በዓሉ ፍፁም ሰላማዊና እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ማድረግ የሁሉም ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው በበኩላቸው ለኢሬቻ በዓል በርካታ ህዝብ በክፍለ ከተማው አልፎ ወደ ከተማው የሚገባ በመሆኑ ከብሎክ ጀምሮ ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠር የሚመጡ እንግዶችን በተገቢው መልኩ ተቀብሎ መሸኘት ፣ ተግባራትን በመከፋፈል በባለቤትነት ስሜት መምራት ፣ አካባቢን ውብና ፅዱ ማድረግ ፣ የሽብርቅ ስራዎችን ከወዲሁ መጨረስ ፣ በዓሉን በመጠቀም ህገ-ወጥ ተግባራት እንዳይፈፀሙ በንቃት መጠበቅ እንደሚገባ ተናግረዋል

Related Post

ልዩ ዜና