የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በመደበኛነት እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ከክፍለ ከተማና ከወረዳ አመራሮች ጋር ገምግሟል።
አስተዳደሩ ስራ ዕድል ፈጠራ ፣ የጤና መድህን ተጠቃሚዎች ምዝገባ ያለበት ደረጃ እንዲሁም ሌሎች የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች ያሉበትን ሁኔታ በዛሬው ዕለት ገምግሟል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት በክፍለ ከተማው አስተዳደር የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ልማት ለማረጋገጥ የሚወርዱ ተግባራትን በጊዜ የለኝም መንፈስ መተግበር እንደሚገባ የገለፁ ሲሆን አመራሩ ስራዎችን አስተሳስሮ በመስራት የሚወርዱ ተግባራት በልዩ ትኩረት በመፈፀም በተቀመጠው እቅድ መተግበር እንደሚገባ ገልፀዋል::
የክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው በበኩላቸው የሚከናወኑ ተግባራት መሠረታዊ የህብረተሰቡን ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ የሚያስችል በመሆኑ አሁናዊ ሁኔታን የተረዳ የአመራር ስምሪት በመስጠት የሚፈጠሩ ንቅናቄዎችን ወደ እድል የሚቀይር አመራር መሆን ይገባል በማለት ገልፀው በክፍለ ከተማው የወጣቶችና ሴቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ዕውን ለማድረግ የሚፈጠሩ የስራ ዕድሎች በእድገት ተኮር ዘርፎች ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።