በበአስተዳደሩ በክፍለ ከተማው የሚገኙ ኢንዱስትሪ ምርትና ምርታማነታቸውን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ተገለጸ።
(ጉለሌ ኮሙኒኬሽን ፣ 11 -04 -2018 ዓ.ም )
በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ምርትና ምርታማነታቸውን ከማረጋገጥ እያከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ክትትል ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የመስክ ምልከታ የአዲስ አበባ ከተማ ሱፐርቪዥን ቡድን ግብረ-መልስ ዙሪያ ውይይት አካሄደ።
የሱፐርቪዥን ቡድኑ በክፍለ ከተማና በወረዳ በተግባር ወርዶ ያያቸውን በጠንካራ የነበሩ ስራዎች በክፍተት የያቸውና ቢሰተካከሉ የሚሉትን ውይይት ተደርጎበታል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት በከተማ የተላከው ሱፐርቪዥኑ ቡድን ላከናወነው ድጋፍና ክትትል ምስጋናቸውን አቅርበው ቡድኑ ለሰጠው ግብረ መልስ ለቀጣይ ስራዎች መሻሻል ጠቃሚ ግብዓትና ተሞክሮ የተገኘበት ነው ያሉ ሲሆን የኢንዱስትሪ ምርትና ምርታማነታቸው ለማረጋገጥ ይሰራል ብለዋል።
የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ማነቆዎች ደረጃ በደረጃ በመፍታት ተተኪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት የውጭ ምንዛሪ ፤ ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ ከሚልኩ አምራቾች የውጭ ምንዛሬ ከማዳን እንዲሁም ለበርካታ ዜጎቻችን ዘላቂና አስተማማኝ የስራ ዕድል ለመፍጠር እንሰራለን ብለዋል።
የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው በበኩላቸው የአምራች ኢንዱስትሪዎች አምራቾችን የማነቃቃት ተግባር በማድረግ ተወዳዳሪ ጥራት ያለው ምርት የማምረት ስራ መስራት መሆኑን ገልጸው የግብዓትና የጥሬ ዕቃ ፣ የገበያ ትስስር ፣ የማምረቻ ቦታ እጥረት ያነሷቸውን ችግር ደረጃ በደረጃ የመፍታት ስራ ይሰራል ብለዋል።