የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር "በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ" በሚል መርህ የተቀመጡ ግቦች በባለፉት ጊዜያት የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀምን በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አካሂዷል።

user 25-Dec-2025 ወቅታዊ ጉዳይ

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር "በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ" በሚል መርህ የተቀመጡ ግቦች በባለፉት ጊዜያት የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀምን በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አካሂዷል።

የውይይት መድረኩን የመሩት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የተቀመጡ የኢኒሼቲቭ ግቦችና አቅጣጫዎች በክፍለ ከተማው ተግባራዊ በማድረግ የህብረተሰባችንን ሁለንተናዊ ልማትና ብልጽግና ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ በበኩላቸው የኢኒሼቲቭ ግቦች ላይ የሚከናወኑ ተግባራትን አመራሩ በዕቅዱ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ በመያዝ የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማሳደግ የነዋሪውን ህይወት ከመቀየር አኳያ የማይተካ ሚና እንዳለው ለማሳካት እያደረገ በመግለፅ ወረዳዎች ውጤታማ ተቀራራቢ አፈፃፀም እንዲኖራቸው መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የስራ ዕድል ፈጠራ፣የሌማት ትሩፋት እና የተረጂነት ቅነሳ ዕቅድን ከመደበኛ ተግባራት ጋር አቀናጂቶ በመስራት ዕቅዱን ማሳካት እንደሚገባ ከመድረኩ አቅጣጫ ተቀምጧል።

Related Post

ልዩ ዜና