በቀበና ወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ላይ ለተሰማሩ ባለሙያዎችና ሰራተኞች የማበረታታትና የእራት ግብዣ መርሃ ግብር ተካሄደ።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በቀበና የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራ ፕሮጀክት ለተሰማሩ ባለሙያዎችና ሰራተኞች የእራት ግብዣ መርሃ ግብር በማካሄድ የማበረታታት ስራ ተሰርቷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የልዩ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳርዳር ብርሀኑ ለከተማችን ሁለንተናዊ ለውጥና ብልፅግና ጉልህ ሚና የሚኖረውን የቀበና ወንዝ ዳርቻ ላይ አሻራችሁን እያኖራችሁ የምትገኙ ባለሙያዎችንና ሰራተኞችን ማበረታታት የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ሊሆን ይገባል ያሉ ሲሆን አሻራቸውን እያኖሩ ለሚገኙ ባለሙያዎችንና ሰራተኞች የአብሮነት እራት ግብዣ አካሄደዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ምስጋናው በበኩላቸው ለዘመናት የቆሻሻ መጣያና የጤና ጠንቅ ሆኖ ተዘንግቶ የቆየውን የወንዝ ዳርቻ ልማት ከተጀመረ አንስቶ እስካሁን የክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ባለሙያዎችንና ሰራተኞችን በማበረታታት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።
የቀበና የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራው ለ24 ሰዓት በሳምንት ደግሞ ለ7 ቀን ያለማቋረጥ የሥራ ባህል በላቀ ትጋት በመስራት ላይ ይገኛል ።