በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የአንድ ማዕከል የሰላም ሰራዊት ስምሪት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

user 26-Sep-2025 ወቅታዊ ጉዳይ

በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የአንድ ማዕከል የሰላም ሰራዊት ስምሪት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

 

ጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ የአካባቢውን ሰላም በንቃት እያስጠበቀ ለሚገኘው የአንድ ማዕከል የሰላም ሰራዊት ስምሪት በተለያዩ ወረዳዎች ተዘዋውረው ምልከታ አድርገዋል።

እንዲሁም በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ህዝባዊ የሰላም ሰራዊት አባላት የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላትን ምክንያት በማድረግ በአንድ ማዕከል ስምሪት በመውሰድ የአካባቢያቸውን ሰላም እያስጠበቁ የሚገኙትን አበረታተዋል።

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ ሁለቱ የአደባባይ በዓላት እስኪጠናቀቁና ከተጠናቀቁም በኋላ ሰላምን የማስጠበቅ ስራው ሊጠናከር እንደሚገባ ገልፀው፤ ሰላምን ማረጋገጥ የሚቻለው በራሱ በህዝቡ አማካኝነት መሆኑን በማንሳት ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ የሰላም ሰራዊቱ ከፀጥታ አካላትና ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት አካባቢውን በንቃት ሊጠብቅ እንደሚገባ ተናግረዋል።

Related Post

ልዩ ዜና