የሁሉንም ህብረተሰብ የሰላም ባለቤትነት ተሳትፎውን በማሳደግ የክፍለ ከተማው ሰላምና ጸጥታ በማረጋገጥ ውጤታማ ስራ መሰራቱ ተገለፀ።

user 23-Dec-2025 ማህበራዊ ጉዳዮች

የሁሉንም ህብረተሰብ የሰላም ባለቤትነት ተሳትፎውን በማሳደግ የክፍለ ከተማው ሰላምና ጸጥታ በማረጋገጥ ውጤታማ ስራ መሰራቱ ተገለፀ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ለክፍለ ከተማው ፖሊስ ኮሚኒቲ እና ከ10ሩም ወረዳ ለተወጣጡ የሰላም ሰራዊት አደረጃጀቶች በጸጥታ አጠባበቅና በበጎ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።

በስልጠናው ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት አስተዳደሩ ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ እና በማደራጀት የአካባቢውን እንዲጠብቅ ህዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓላት ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቁ ማድረግ ፣የወንጀል ድርጊቶችን በመለየት እና መከላከል በቅንጅት ተባብሮ በመስራት የነዋሪውን ደህንነት በተሻለ መልኩ ማረጋገጥ የተቻለበት መሆኑን ገልጸው ሰልጣኞች ያገኙትን ግንዛቤ ተጠቅመው የክፍለ ከተማውን ሰላምና ጸጥታ ማስጠበቅ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ፈይሳ በበኩላቸው ለክፍለ ከተማችን ሰላም መጠበቅ በተለይ የሰላም ሰራዊቱ የነበራቸውን ሚና አመስግነው በቀጣይም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለአከባቢው ሰላም መጠበቅ ባለቤት ሆኖ በቅንጅት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

Related Post

ልዩ ዜና