የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸሙንና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅዱን ከአጠቃላይ ከክፍለ ከተማ ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄዷል።
አስተዳደሩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በመንግስት ስራዎች ያከናወናቸው የሰላምና ጸጥታ ስራዎች ፣ የፕሮጀክት አፈጻጸም ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ የማሻሻል በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን የተሰራበት፣ ፍትሃዊ የወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ፣ የገቢ አሰባሰብና አፈጻጸም ፣ በኑሮ ውድነት የማረጋጋት ስራዎች ፣ በከተማ ግብርና የሌማት ትሩፋት ስራዎች ፣ በትምህርትና በጤና ዘርፍ ፣ የበጎ ፈቃድ ተግባራት ፣ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ፣ የከተማ ውበትና የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ፣ የተለያዩ የንቅናቄ ተግባራት በውጤታማነት ማከናወኑን በሪፖርቱ ተገልጿል ።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት አስተዳደሩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በርካታ ውጤታማ ስራዎችን መስራት የተቻለ መሆኑን ለዚህም የመንግስት ሰራተኛው በምንሰራቸው ተግባራት ሚናው የላቀ እንደነበር ገልጸው በቀጣይ በጀት ዓመት ተግባራት ላይ የሚቀሩ ስራዎች በትኩረት በመያዝ በዕቅድ መስራት ፣ ቅንጅታዊ አሰራር ፣የድጋፍና ክትትል ስራዎች ላይ ክፍተቶች መኖራቸውን በማረም ወደ ከፍታ መውጣት እንደሚገባ ገልጸዋል።