የ90 ቀናት እቅድ ከተለመደው የእቅድ አተገባበር በተጨማሪ ውጤት በሚያመጣ መልኩ በመተግበር የማህበረሰብ እርካታ ማሳደግ ተገቢ እንደሆነ ተገለጸ።
የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው የወረዳ 1 እና ወረዳ 2 አስተዳደር አጠቃላይ አመራሮች በተገኙበት የ90 ቀናት እቅድ አፈጻጸም የተደረሰበትን ደረጃ ገምግመዋል።
ሃላፊው 2ቱን ወረዳዎች የ9 ቀን እቅዱ በውጤት እስከሚጠናቀቅ የሚደግፉ ሲሆን የተሰሩ ስራዎችን በቀረበላቸው ሪፖርት መሰረት የነበሩ ጉድለቶችንና ጥንካሬዎችን አስቀምጠዋል።
በ90 ቀናት የተያዙ እያንዳንዱን አጠቃላይ ግቦችን እና ተግባር ለማጠናቀቅ እና ለማሳካት እውነተኛ የጊዜ መስመር በመከተል ትኩረት የሚሰጠውን ተግባራትን ቅድሚያ በመስጠት እና ቁልፍ ግቦችን ለማሳካት በትኩረት ይዞ መስረት እንደሚገባም አንስተዋል።