የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በወቅታዊና በመደበኛነት አስተዳደሩ በሚያከናውናቸው ተግባራት አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት አድርጓል።
የክፍለ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በ2017 በጀት ዓመት በቀሪ ወራት በሚከናወኑ ተግባራትና፣ በተለያዩ የበጀት ወጪዎችና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጓል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት አስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በመደበኛነትና በዕቅድ ተግባራትን ይዞ በመስራት ላይ ይገኛል ያሉ ሲሆን በቀሪ ወራት የሚከናወኑ ተግባራት በማጠናቀቅና መረጃዎችን በማደራጀት ላይ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
አገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል የህብረተሰቡን እንግልትን በመቀነስ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የምንቀርፍበት ዋነኛ መፍትሄ በመሆኑ አሁንም በትኩረት ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
ካቢኔው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ የቀረቡለትን በጀቶችን በማጽደቅ አጠናቋል።