በኮሪደር ልማቱ አካባቢ የሚደረግ የጽዳት ዘመቻ ህብረተሰቡ የጽዳትና የልማቱ ባለቤት ለማድረግ እንደሆነ ተገለጸ።

user 22-Aug-2025 ማህበራዊ ጉዳዮች

በኮሪደር ልማቱ አካባቢ የሚደረግ የጽዳት ዘመቻ ህብረተሰቡ የጽዳትና የልማቱ ባለቤት ለማድረግ እንደሆነ ተገለጸ።

‎በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከ6 ኪሎ -በሽሮ ሜዳ - እንጦጦ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የጽዳት ዘመቻ መርሃ ግብር ተካሄዷል።

በጽዳት ዘመቻው ላይ በመገኘት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ‎የጉለሌ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሰለ ይትባረክ በኮሪደር ልማቱ አካባቢ የሚደረግ የጽዳት ዘመቻ ህብረተሰቡን ባለቤት ከማድረግ በተጨማሪ ውብና ጽዱ አዲስ አበባን ለመፍጠር ከተያዘው እቅድ አንዱ ነው ብለዋል።

‎ኃላፊው አክለውም የኮሪደር ልማቱን ከቆሻሻ በመጠበቅ፤በባለቤትነት በመያዝ፣ጽዳትን ባህል በማድረግ የትኛውንም ልማት በጋራ በማከናወን በአንድነት ሆነን ለለውጥና ውጤታማነት እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።

‎ በክፍለ ከተማው ህብረተሰቡ ጽዳትን ባህል እንዲያደርግ የተለያዩ የጽዳት ንቅናቄ በማድረግ ላይ ይገኛል በዛሬው ዕለትም በኮሪደር ልማት በሚከናወንበት ህብረተሰቡ የጽዳት ባለቤትና የልማቱ ባለቤት እንዲሆን የጽዳት ዘመቻ አካሄደናል ብለዋል።

‎በኮሪደር ልማቱ በሚካሄድበት አካባቢ በተደረገው የጽዳት ዘመቻ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ ነዋሪዎችና እንዲሁም የጽዳት ባለሙያዎች የተሳተፉበት የፅዳት ዘመቻ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት አካባቢ የጽዳት ዘመቻው ተካሂዷል::

Related Post

ልዩ ዜና