የመማር ማስተማር ሂደቱ ሰላማዊ እንዲሆን ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳተፎ ማድረግ እንዳለበት ተገለጸ።

user 07-Nov-2025 ማህበራዊ ጉዳዮች

የመማር ማስተማር ሂደቱ ሰላማዊ እንዲሆን ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳተፎ ማድረግ እንዳለበት ተገለጸ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የተማሪዎችን ዉጤት ለማሻሻል እና የመማር ማስተማር ሂደቱ ሰላማዊ በሆነ አግባብ ማስኬድ እንዲቻል ፣የ20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን አከባበር እንዲሁም በ12ኛ ክፍል የተማሪዎች ውጤት ማላቂያ ስትራቴጂክ ከዘርፉ አመራሮችና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት አካሄደ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊና የዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ ሀብታሙ ደረጀ እንደተናገሩት በክፍለ ከተማው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራዉ በሚፈለገው ልክ እንዲሆን የተማሪ ወላጆችን ፣ ተማሪዎችን እና የጸጥታ አካላትን የላቀ አስተዋጽኦ የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም አካል የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል መምራንና ወላጆች አስፈላጊዉን ክትትል ማድረግ እንዳለባቸው እና ተማሪዎች በርትተው በማጥናት ዉጤታማ መሆን እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

Related Post

ልዩ ዜና