በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት ከ5.2 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ተገንብተዉ ለአገልግሎት ክፍት ከተደረጉ 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች ተመረቁ።
(ጉለሌ ኮሙኒኬሽን ፣ 11 -11 -2017 ዓ.ም)
በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳር በ2017 በጀት ዓመት የተገነቡ የትምህርት ተቋማት መሠረተ ልማቶች ግንባታ ተመርቀው አገልግሎት መስጠት ጀመሩ።
በክፍለ ከተማው አስተዳደር በወረዳ 9 የሚገኘው የጀነራል ታደሰ ብሩ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት G+2 የክፍል ማስፋፊያ ህንጻ እና በወረዳ 10 የሚገኘው ምዕራፍ ቁ.2 ቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል።
በምርቃት መርሃ ግብሩ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት የክፍለ ከተማው አስተዳደር የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን በማቃለል ተጠቃሚነቱን ይበልጥ ለሚያረጋገጥ ለልማት ፕሮጀክቶች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ያሉ ሲሆን በክፍለ ከተማችን በመገንባት ላይ የሚገኙት የልማት ፕሮጀክቶች የዚሁ ጥረት አካል ናቸው ብለዋል፡፡