በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2018 የችግኝ እንክብካቤ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄደ።
በክፍለ ከተማው የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት በክረምት ወራት በሁለተኛ ምዕራፍ 7ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ መርሀ ግብር የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በእንጦጦ ፓርክ አካሄዷል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ የዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊና የምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማሩ መንግስቱ እንደተናገሩት እንደሀገር የተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ ልማት የተስተካከለ የዝናብ ስርጭት እንዲኖር፣ ለኑሮ ተስማሚ የሆነ አካባቢ ለመፍጠር፣ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግና፣ የኢኮኖሚ ጥቅም ለማግኘት ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ችግኝ ተክሎ ማሳደግ የዘውትር ተግባራችን መሆን አለበት ሲሉ ተናግረዋል።
የክፍለ ከተማው የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ኤደን ካሳ በበኩላቸው በክረምት የተተከሉ ችግኞች በበጋው ወቅት ውሃ በማጠጣትና በመንከባከብ የጽድቀት መጠናቸውን ማሳደግና ለፍሬ ማብቃት ከሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች እንደሚጠበቅም ገልፀዋል።
የክፍለ ከተማው ፕላን ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አማን አንዱዓለም በበኩላቸው ጽ/ቤቱ ከሚያከናውነው መደበኛ ተግባር ጎን ለጎን ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በርካታ ተግባር እያከናወነ ይገኛል የዛሬው ችግኝ ተከላ የዚሁ አካል ነው ብለዋል።