የኢትዮጵያ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ብሔራዊ ኩራታችን ነው ።
(ጉለሌ ኮሙኒኬሽን ፣03 -10- 2017 ዓ.ም )
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የቦንድ ግዥ ንቅናቄ ማጠቃለያ ፕሮግራም ተከናውኗል።
በንቅናቄ መድረኩ በክብር እንግድነት የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የስራ ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ ባስተላለፉት መልክት በዓባይ ወንዝ ዙሪያ ይነገሩ የነበሩ ጎታች አስተሳሰቦችና ትርክቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስቀረት መቻሉን ፤ በአለም ደረጃ ኢትዬጵያን በማኮሰስና በማስፈራራት ህዳሴያችን እንዳንገነባ የማደናቀፍ ሴራን በማክሸፍ የተጀመረውን ፕሮጀክት ከዳር ለማድረስ ጥቂት ቀርቶናል ብለዋል ።
እንደሀገር በርካታ ሰው ተኮር ኘሮጀክቶችን ጀምረን በአጭር ጊዜ መፈፀምና ቃልን በተግባር ማሳየት የቻልንበት ነው ሲሉ የገለፁት አቶ ሰለሞን ታደሰ በተጀመረው የቦንድ ሽያጭ የንቅናቄ መርሃ ግብር የወረዳው ማህበረሰብ የተለመደውን የአንድነት፣ የሰላም የአብሮነት ተምሳሌት የሆነውን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ቦንድ ግዢ ላይ ተሳታፊነቱን በማረጋገጥ የተገባደደውን ግንባታ ከፍጻሜ ማድረስ እንደሚገባ አቶ ሰለሞን አሳስበዋል ፡፡