በከተማችን እየተመዘገበ የሚገኘው አንፀባራቂ ድል የጠራ እሳቤያችን እና የህዝብና የመንግስት ቅንጅታዊ ርብርብ ውጤት ነው።

user 27-Aug-2025 ማህበራዊ ጉዳዮች

በከተማችን እየተመዘገበ የሚገኘው አንፀባራቂ ድል የጠራ እሳቤያችን እና የህዝብና የመንግስት ቅንጅታዊ ርብርብ ውጤት ነው።

የጉለሌ ክ/ከተማ ነዋሪዎችም የኮሪደር ልማቱ እንዲሳካ ከክ/ከተማው አስተዳደር ጎን በመሰለፍ ንቁ ተሳትፎ በማድረጋቸው በጉስቁልና ይታወቁ የነበሩ አካባቢዎችን የለውጥ እና የውበት ምሳሌ እያደረጉ ይገኛሉ።

የሽሮሜዳ አካባቢ ነዋሪዎችም የመሬት ይዞታቸው ለልማት ሲፈለግ በቅንነት በመተባበር ለከተማችን ድምቀት ለቱሪስት ፍሰቱ ደግሞ ምቹ የሆነች ሽሮ ሜዳን ዕውን እንድትሆን የበኩላቸውን አበርክተዋል።

በሽሮ ሜዳ የኮሪደር ልማት አረንጓዴ ልማት፣ የታክሲ ማቆሚያዎች ፣ የእግረኛ መንገድ፣ በቂ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች እንዲሁም ሌሎች መሰረተ ልማቶች ደረጃቸውን ጠብቀው ለኑሮም ፣ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን ለማሳለጥም ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።

ወጣቶች እና ህፃናት ብሩህ አእምሮና ጠንካራ ሰውነት እንዲኖራቸው የሚያስችሉ የወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና ለህጻናት የቀዳማይ ልጅነት ፕሮጀክቶችም በኮሪደር ልማቱ ተገንብተዋል።

በሽሮ ሜዳ እና አካባቢው የተገነባው የኮሪደር ልማት ሰፊ የአስፋልት መንገድ ፣ ደረጃውን የጠበቁ የብስክሌት እና የእግረኛ መንገዶች ፣ 11 የታክሲ እና የአውቶብስ መጫኛና ማውረጃ ቦታዎችንም ይዟል።

ፕሮጀክቱ 20 አረንጓዴ መናፈሻ ቦታዎች ፣ ሁለት ፕላዛዎች ፣ 10 የህፃናት መጫዎቻዎች ፣ ሰባት የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ፣ ዘጠኝ መፀዳጃ ቤቶች ፣ በመንግስት እና በግሉ ዘርፍ የተገነቡ ሁለት ዘመናዊ ተርሚናሎች ፣ ነባር እና አዲሶቹን ጨምሮ 1521 በላይ ሱቆች ያሉት ሲሆን ከ15 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች ጊዚያዊ እና ቋሚ የስራ እድል መፍጠር ችሏል።

የጉለሌ ክ/ከተማ ህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍም እነዚህ ፕሮጀክቶች ይበልጥ እንዲሰፉ ተነሳሽነትን ከፍ ለማድረግ የሽሮ ሜዳን የኮሪደር ልማት ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አስጎብኝቷል።

በጉብኝቱ ላይ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን ፣አርቲስቶች፣ በጎ ማህበረሰብ አንቂዎች፣ ባለሀብቶች፣ ወጣቶችና ሴቶች እንዲሁም አባገዳዎችንና ሀደስንቄዎች የተሳተፉ ሲሆን በተመለከቱት ልማት መደመማቸውን ገልፀዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ቃሉን በማክበር ጥያቄዎቻቸውን ሳይውል ሳያድር በአጭር ጊዜ እየመለሰ እንደሚገኝ ሽሮሜዳ ማሳያ መሆኗን የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

Related Post

ልዩ ዜና