በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋጥ የመስሪያ ቦታዎችን ህጋዊነት የማስጠበቅ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

user 03-Nov-2025 ማህበራዊ ጉዳዮች

በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋጥ የመስሪያ ቦታዎችን ህጋዊነት የማስጠበቅ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ መስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር በህገ ወጥ መንገድ የተያዙና ከ5 ዓመት በላይ የሆናቸውን በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ መስሪያ ቦታዎችን በግብረ ሃይል ማስለቀቁን ገለጸ።

በመግለጫቸው ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ መስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም አያሌው እንደተናገሩት የክፍለ ከተማው አስተዳደር የሴቶችና የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት አየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው ያለ አግባብ የተያዙ 761 ካሬ.ሜ መስሪያ ቦታዎች በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙትን የማስለቀቅ ስራ በግብረ ሃይል ተሰርቷል ብለዋል ።

የመልካም አስተዳደር ችግር ያለባቸውና ያለ አግባብ የተያዙ መስሪያ ቦታዎች ማስለቀቅም ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በመግለጽ የተለቀቁ መስሪያ ቦታዎችን በመመሪያ መሠረት የተደራጁና ህጋዊነታቸው በሚመለከታቸው አካል ለተረጋገጠ በግልጽነት የማስተላለፍ ስራ ይሰራል ብለዋል።

የክፍለ ከተማው አስተዳደር የወጣቶችንና ሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል በቀጣይም በዘርፉ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮች በጋራ መዋጋት እንደሚገባ ተገልጿል።

Related Post

ልዩ ዜና