#በጎ_ፈቃደኝነት_ለማህበረሰብ_ለውጥ !! "

user 28-Aug-2025 ማህበራዊ ጉዳዮች

#በጎ_ፈቃደኝነት_ለማህበረሰብ_ለውጥ !! "

የጤና ባለሙያዎች የህብረተሰቡን ጤና ከመጠበቅ ባሻገር ማህበራዊ ሃላፊነትን ለመወጣት የሚያደርጉት ተግባራት አጠናክረው ማስቀጠል እንዳለባቸው ተገለጸ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ባለሙያዎች ጋር በጋራ በመሆን በክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር የአቅመ ደካማ ቤት ዕድሳት መርሃ ግብር በክፍለ ከተማው ወረዳ 4 አስጀመረ።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ጎዴቦ እንደተናገሩት በክፍለ ከተማው የተለያዩ ተቋማትንና ግለሰቦችን በማስተባበር የክረምት የተለያዩ መርሃ ግብሮችን እያከናወንን እንገኛለን ያሉ ሲሆን በዛሬው ዕለት የጤና ጽ/ቤት ከባለሙያዎች ጋር በመተባበር ያከናወነው ተግባር ሊቀጥል የሚገባና ለሌሎች አርዓያ የሚሆን ተግባር ነው ብለዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሄለን አሰፋ በበኩላቸው የጤና ባለሙያዎች የህብረተሰቡን ጤና ከመጠበቅ ባለፈ ማህበራዊ ኃላፊነት በመወጣት በርካታ ተግባራትን እያከናወኑ ይገኛል በዛሬው ዕለት ያስጀመርነው የአቅመ ደካማ ቤት ዕድሳት ለዚህ ማሳያ ነው ብለዋል።

#ደግ_ልብ_ድንበር_የለውም !!

Related Post

ልዩ ዜና