በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም (ECD) እና የወጣቶች የስፖርት ማዝወተሪያ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለተጠቃሚዎች ተላለፉ።

user 08-Jul-2025 ልማት

በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም (ECD) እና የወጣቶች የስፖርት ማዝወተሪያ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለተጠቃሚዎች ተላለፉ።

በምርቃት መርሃ ግብሩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጀማሉ ጀምበር እንደተናገሩት ከተማ አስተዳደሩ በርካታ ሰው ተኮር የሆኑ የልማት ፕሮጀክቶች በመስራት የህብረተሰቡን ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ላይ ይገኛል ያሉ ሲሆን በተጨማሪ እነዚህን መሠረተ ልማት ማድነቅ፣ ማበረታታት እና መንከባከብ አለብን በተመሳሳይ የኑሮ ውድነትን የሚቀርፋ ሰው ተኮር ስራዎች እና ስራ እድል ፈጠራ የህዝብ ተጠቃሚነት ላይ እንደ ከተማ የተለያዩ ስራዎች በስፋት እንደሚሰሩ ገልጸዋል ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት በክፍለ ከተማው ሰው ተኮር ችግር ፈቺ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ እንደሚገኝ በመግለጽ የክፍለ ከተማው አስተዳደር ለቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ተግባራዊ ዕውን ለማድረግ ዘመናዊ የህጻናት ማቆያ (ዴይ ኬር) ፣ዘመናዊ የወጣቶች ስፖርት ማዝወተሪያ በዛሬው ዕለት ክፍት አድርገናል

ለፕሮጀክቶቹ መሳካት አስተዋፅኦ ለነበራቸው አካላት ሁሉ በክፍለ ከተማ አስተዳደሩና በነዋሪው ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Related Post

ልዩ ዜና