ክፍለ ከተማችንን በአረንጓዴ ልማት ተግባራትና የተቀናጀ ሞዴል ብሎክ በመፍጠር ውብና ማራኪ እናደርጋታለን !!
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) በተቀመጡ አቅጣጫ ባለ ሁለት ግቦች የተቀናጀ ሞዴል አካባቢዎች ላይ ለመፍጠር የሚያችል ጉብኝት ተካሄደ።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ፣ የአዲስ አበባ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ይመር ከበደ ፣ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ጎዴቦ ፣ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚኪያስ ቦንኬ ጨምሮ የወረዳ አመራሮች በተገኙበት ጉብኝት አካሄዷል።
በማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ መልዕክት ያስተላለፉት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት ከተማችን አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብና ማራኪ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል እንደ ክፍለ ከተማ ሞዴል አካባቢዎችን የመፍጠር በቅንጅት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን ገልጸው በዛሬው ጉብኝት በአረንጓዴ ልማት ስራዎችና በቀዳማይ ልጅነት መጫወቻ ስፍራ በተለያዩ ወረዳዎች በማስፋት የክፍለ ከተማችንን ገጽታ ለመቀየር ያለመ ነው ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ይመር ከበደ የተቀናጀ ሞዴል መንደሩን እውን ለማድረግ የክፍለ ከተማው አመራሮች ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተቀራርበው እየሰሩ በመሆናቸው ተሳክቶ እንደምናየው ተስፋ አለኝ ሲሉ ተናግረዋል::
የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ጎዴቦ በበኩላቸው መዲናችን አዲስ አበባን ወብ፣ ፅዱና ማራኪ ለማድረግ እየተሰራ ያለው ስራ ውጤት እየተገኘበት መሆኑን ገልፀው የተቀናጀ ሞዴል መንደርን ለመፍጠር ህብረተሰቡን ተሳታፊ በማድረግ በትብብር መስራት ይገባል ብለዋል::