የአገልግሎት ቀንን ለተገልጋይ ብቻ

user 10-Dec-2025 ልማት

የአገልግሎት ቀንን ለተገልጋይ ብቻ❗

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የአገልግሎት ቀንን ለተገልጋይ ብቻ የሚለውን አቋም ይዞ በአንድ ማዕከል ህዝቡን በግልፅነት ማገልገል ከጀመረ ሰነባብቷል።

የአንድ ማዕከል አገልግሎቱም ረቡዕና ዓርብን ማዕከል አድርጎ በአስተዳደራችን ባሉ በሁሉም ጽ/ቤቶች እየተሰጠ ሲሆን ለተገልጋይ ክብር ሲባል የደንበኛ መረጃ መስጫ ማዕከላትንም ማደራጀት ተችሏል። በዚህም በርካታ የህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ አግኝተዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ ፣ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና ስራና ክህሎት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ ጨምሮ ሌሎች የጽ/ቤት ኃላፊዎች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛል።

በአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጡም አንድ ዓይነት ጉዳይ ያላቸውን በጋራ ምላሽ በመስጠት፣ ወረፋን በመጠበቅ የሚጠፋ ጊዜን በመቆጠብ፣ ብልሹ አሰራርን ለማስወገድና ግልፀኝነትን ለመፍጠር ፣ እንዲሁም በቢሮ ያልተገደበ አገልግሎት በመስጠት አንዱ ለአንዱ ምስክር የሚሆንበትን አሰራርም በመፍጠር የተገልጋዩን ህብረተሰብ አንገብጋቢ ጥያቄዎች ለመመለስ በክፍለ ከተማው አስተዳደር በከፍተኛ ትኩረት እየሰራ ይገኛል።

ተገልጋዮቻችን እኛ የጀመርነው ግልፅ የሆነ የህዝብ አገልግሎት ግልፀኝነቱ ፣ ፍትሐዊነቱና ፍጥነቱ የሚረጋገጠው በእናንተ እገዛ ነውና ሁሌም እገዛችሁ አይለየን።

ዛሬም ኑ ልናገለግላችሁ ተዘጋጅተናል ።

መልእክታችን ነው!!

Related Post

ልዩ ዜና