በክፍለ ከተማው የወጣቶችና የሴቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ተገለጸ።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በ11 ወራት የስራ ዕድል ፈጠራና የንቅናቄ ተግባራት ዕቅድ አፈጻጸም የአዲስ አበባ ከተማ ስራ ክህሎት ቡድን ግብረ-መልስ ዙሪያ ውይይት አካሄደ።
የክፍለ ከተማው አስተዳደር በ2017 ዓ.ም የ11 ወራት የስራ ዕድል ፈጠራ ተግባራት ዕቅድ አፈፃፀም የሱፐርቪዥን ግብረ-መልስን ከክፍለ ከተማና ከወረዳ አመራሮች ጋር ገምግሟል።
የሱፐርቪዥን ቡድኑ በክፍለ ከተማና በወረዳ በሰነድና በተግባር በሴቶችና በወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራና ወርዶ ያያቸውን በጠንካራ የነበሩ ስራዎች በክፍተት የያቸውና ቢሰተካከሉ የሚሉትን በሰነድና በተግባር አቅርቦ ውይይት ተደርጎበታል።