#አንድም_እናት_በደም_እጦት_መሞት_የለባትም !!

user 28-Aug-2025 ማህበራዊ ጉዳዮች

አንድም_እናት_በደም_እጦት_መሞት_የለባትም !!

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሴቶች ፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ከተለያዩ የሴት አደረጃጀቶች ጋር በክረምት በጎ ፈቃድ ተግባር አንዱ የሆነው የደም ልገሳ ፕሮግራም አካሄዷል።

ጽ/ቤቱ በክረምት በጎ ፈቃድ " አንድም እህት ፣ እናት በደም እጦት አትሞትም " በሚል መሪ ቃል ከ10ሩም ወረዳ የተወጣጡ ሴቶች የደም ልገሳ መርሃ ግብር አከናውኗል ።

በመርሃ ግብሩ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ጎዴቦ እንደተናገሩት አስተዳደሩ በክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር ሰው ተኮር የሆኑ ተግባራት በማከናወን የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ላይ እንገኛለን በዛሬው ዕለትም ከተለያዩ አደረጃጀቶች የተወጣጡ የክፍለ ከተማችን ሴቶች በጎነትን ባህል በማድረግ የደም ልገሳ አከናውነዋል ብለዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ እየሩሳሌም በትሩ እንደተናገሩት ሴቶች በክፍለ ከተማው በሚከናወኑ ተግባራት የራሳቸውን አስተዋጽዖ እያበረከቱ እንደሚገኝ ገልጸው በክረምት መርሃ ግብር አንዱ የሆነው የደም ልገሳ ፕሮግራም መርሃ ግብር አካሄደናል ብለዋል።

የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ሰብሳቢ ወ/ሮ የኔዓለም አየለ በበኩላቸው ሊጉ የሴቶችን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ባሻገር የበጎ ፈቃድ ተግባራት በማከናወን ይገኛል ያሉ ሲሆን የሴት ክንፍ ከሌሎች አደረጃጀቶች ጋር የደም ልገሳ አድርገናል።

በደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ላይ የክፍለ ከተማው ወጣት ሊግ ፣ ሴት ክንፍ ፣ ወጣት ማህበር ፣ ሴቶች ማህበር አባላት የደም ልገሳ መርሃ ግብር አከናውነናል።

Related Post

ልዩ ዜና