የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ስራ ኮሚሽን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር የአቅመ ደካማ የቤት ዕድሳት መርሃ ግብር አካሄደ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ መራጭ ተመራጭና የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደተናገሩት ኮሚሽን መስሪያ ቤቱ ከሚያከናውነው መደበኛ ተግባሩ በተጨማሪ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በትኩረት እየሰራ ይገኛል በዛሬ ዕለትም የተለያዩ ማህበራትን በማስተባበር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት አስጀምረናል በአጭር ቀናት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ እድሳቱን በማጠናቀቅ ያስረክባል ብለዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ መኩሪያ ጉሩሙ በበኩላቸው ምክር ቤቱ የህዝቡ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች እንዲቀረፉ ከሚያደርገው የክትትልና ቁጥጥር ስራ በተጨማሪ በክረምት ቤት ዕድሳት ፕሮግራም በስፋት በመሳተፍ ላይ እንደሚገኝ እና በዚህ አመትም የአቅመ ደካማ ቤቶችን ለማደስ ዝግጅት ማድረጉን ገልጸዋል።