"የዛሬ አመራሮች ኢትዮጵያ ከውድቀት ያነሳችሁ ትውልድ ናችሁ በዚህም ልትኮሩ ይገባል ። " :- ሙዓዛ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለአጠቃላይ ለክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች በአመራር ጥበብ እና በአመራር ውጤማነት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ ።
ስልጠናውን የሰጡት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ሙዓዛ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንደተናገሩት ብልጽግና ፓርቲ የትውልድን ጥያቄ የሚመልስ ሆኖ የተቋቋመው አመራሮች ናችሁ ይሄን እሳቤ በመያዝ አመራሩ የሚመራውን ማወቅ ፣ ኢትዮጵያን በመውደድ ፣ የለውጥ አቋም መያዝ ፣ የብልጽግና እሴቶች ማወቅና ለሌሎች በማሳወቅ ፣ ዋጋ በመክፈል ዝግጁ መሆን ፣ የሀገር ሀብት ሰፍሮ ቆጥሮ ማወቅ በሱ ትውልድን መጥቀም ያስፈልጋል በመሆኑም የአመራር ዲሲፕሊን ፣ የእችላለለሁ አመለካከት መገንባት ፣ነገ በፈጣሪ ፣ በታሪክ በትውልድ ተጠያቂ መሆኑ አስቦ መስራት ያስፈልጋል በዚህም አመራሩ እንደ ስንቅ በመያዝ በየቀኑ የገዢ ትርክት ግንባታ ፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ፣ የኢትዮጵያ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ፣ የብልጽግና እሳቤዎች መስራት ይገባል ብለዋል።