ከማህበረሰቡ ጋር በቅንጅት በተከናወኑ ተግባራት ጨለማን ተገን ተደርገዉ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ለመቀነስ የተሰራዉ ስራ አበረታች ውጤት ማስገኘቱ ተገለጸ።

user 16-Jul-2025 ልማት

ከማህበረሰቡ ጋር በቅንጅት በተከናወኑ ተግባራት ጨለማን ተገን ተደርገዉ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ለመቀነስ የተሰራዉ ስራ አበረታች ውጤት ማስገኘቱ ተገለጸ።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በወረዳ 7 የሰላም ሰራዊት የማነቃቃትና የአካባቢን ሰላም ማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባር ፣ በሁሉም ጨለማ ቦታዎች መብራት በማውጣት ወንጀልን መከላከል እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች የጸጥታ አካላት ምልከታ አድርገዋል።

በምልከታው ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት የክፍለ ከተማውን ሁለንተናዊ ሰላም ብልጽግና በማረጋገጥ ስራዎች በቅንጅት በመስራት የሰላም ሰራዊቱ የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ ማስጠበቅ የማንቃት ፣ የተቀናጀ ሞዴል ብሎኮችን በመፍጠር የህብረተሰባችንን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል አስፈላጊ ነው ያሉ ሲሆን ዛሬ በተለያዩ ወረዳዎች የታዩ ለውጦች በማስቀጠል ጉለሌን የሰላምና የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

Related Post

ልዩ ዜና