የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት 12ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በጤና ዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት

user 17-Jul-2025 ማህበራዊ ጉዳዮች

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት 12ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በጤና ዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት

የጤና ዘርፍ ስራችንን ስንመለከት የእናቶችና ህፃናት ጤና ዋናው ተግባር ሲሆን ለ34,407 እናቶች የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ ለ33,895 ወይም 99% ማከናወን ተችሏል፤ የቅድመ ወሊድ ክትትል የጀመሩ እናቶች 8,943 ታቅዶ 8,288 አፈፃፀም 93%፤ በሰለጠነ ባለሙያ የሚሰጠውን የወሊድ አገልግሎት የሚያገኙ እናቶች 7,602 የታቀደ ሲሆን 2722 የእቅዱን 36% ማከናወን ተችሏል፡፡ የድህረ ወሊድ ክትትል አገልግሎት የሚያገኙ እናቶች የእቅዳችን 100% መፈጸም ችለናል፡፡ የነፍሰ ጡር እና

የሚያጠቡ እናቶች የኤች አይ ቪ ምርመራ አገልግሎት የእቅዳችን 100% ፈጽመናል፡፡ ሁሉንም ዓይነት ክትባት አገልግሎት ያገኙ ህፃናት 8,490 ታቅዶ 7,579 የእቅዳችን 89% ተከናውኗል፡፡ የኩፍኝ ክትባት 2 ያገኙ ህጻናት 8,490 ታቅዶ 7,114 የእቅዱን 84% ተፈጽሟል፡፡ የእናቶችና ህፃናት ሞት ከሆስፒታሎች ጋር በቅንጅት በመስራት በጤና ተቋም ላይ ዜሮ ማድረግ ተችሏል፡፡

በሽታ ከመከላከል እና ከመቆጣጠር አኳያ ይበልጥ ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች የኤች አይ ቪ ምክርና ምርመራ እንዲያገኙና እራሳቸውን እንዲያውቁ ለማድርግ 26,308 ታቅዶ 33,175፤ የሁሉም አይነት የቲቢ በሽታ ልየታ መጠን እቅድ 404 ሲሆን 420 በማከናወን ሁለቱንም ከ100% በላይ ተፈጽሟል፡፡ የቲቢ ህክምና ወስደው ሙሉ በሙሉ መዳናቸው የተረጋገጡ ህሙማን መጠን 95% ታቅዶ ክንውን 95% ነው፡፡ የደም ግፊት ልየታ አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ ተገልጋዩች 235,654 ታቅዶ 256,761 አፈፃፀሙ ከ100% በላይ ማከናወን ተችሏል፡፡

መድሃኒትና ህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት አኳያ በጤና ተቋማት የህይወት አድን መድሃኒት አቅርቦት 100% የተሟላ ሲሆን በጤና ተቋማት የመሰረታዊ መድሃኒት አቅርቦት 95% ለማሟላት ታቅዶ 94% ማቅረብ ተችሏል፡፡ በመንግስት ጤና ተቋማት መድሃኒት ታዝዞላቸው የታዘዘውን መድሀኒት 100% ያገኙ (የወሰዱ) ተገልጋዮች 91% ለማድረስ ታቅዶ 91% መፈጸም ተችሏል፡፡

Related Post

ልዩ ዜና