" ሁሉን አቀፍ ህብረተሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት !! "
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የመሠረተ ልማት ስራዎች ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሄደ።
ጽ/ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት የመሠረተ ልማት ስራዎች ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በወረዳ 7 የድጋፍ ግንብና የሰብ ቤዝ ስራዎች አከናውኗል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት ከተማችን አዲስ አበባ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በርካታ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች በማከናወን ላይ ይገኛል በመሆኑም ህብረተሰቡ አካባቢውን በማስዋብ ለኑሮ ምቹ ውብና ተስማሚ በማድረግ ሞዴል አካባቢን በመፍጠር በመስራት አርዓያ የሚሆን ተግባር ማከናወን ይገባል ብለዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለውም በከተማዋ የነዋሪውን ሁለንተናዊ ልማትና ብልጽግና የሚያረጋግጡ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል ከነዚህም አንዱ ሞዴል አካባቢ ፣ ሞዴል መንደርና ሞዴል ቤተሰብ በመፍጠር የከተማዋ ነዋሪዎች ጤናማ በሆነ አካባቢ የመኖር መብታቸውን በመሆኑ ሁሉም ለልማቱ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚኪያስ ቦንኬ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው በበጀት ዓመቱ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን አቅዶ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል በዚህም የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ኃላፊው አክለው ህብረተሰቡ የሞዴል መስፈርቶችን በማሟላት አካባቢውን ውብ ጽዱና ማራኪ በማድረግ የድርሻውን ማበርከት አለበት ብለዋል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣ የብሎክ ኮሚቴዎች ፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።