የቀበና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት የጉለሌ የውበት አክሊል ማሳያ !!
የቀበና ወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ ፣ የጉለሌ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ጎዴቦ ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ፕሮጀክቱ እየተተገበረ በሚገኝባቸው ቦታዎች እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን ተዘዋውረው ምልከታ በማድረግ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በክፍለ ከተማው ወረዳ 1 እና ወረዳ 2 ፕሮጀክቱን በታቀደለት ጊዜ በጥራትና በውጤት ለማጠናቀቅ የሚያስፈልጉ ለስራው መፋጠን ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራት ላይ ያሉ ተግባራት በአካል የተመለከቱ ሲሆን በፍጥነት እየታረሙ እንዲሄዱ በምልከታው ወቅት አቅጣጫ ተቀምጧል።
የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ለከተማዋ አዲስ ገፅታን የሚያላብስ፣ የቱሪስት መዳረሻነሻቷን የሚጨምር እና ለነዋሪዎቿ ውብና ማራኪ ገፅታን የሚያጎናፅፍ ፕሮጀክት በመሆኑን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተገልጿል።