የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል በክፍለ ከተማው ዕውን ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እና ሌሎች አመራሮች በክፍለ ከተማው ወረዳ 8 አስተዳደር እየተገነቡ የሚገኙ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ቢሮ እና መሠረተ ልማት ስራዎች ተዘዋውረው ጎበኙ።
በጉብኝታቸው ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት በክፍለ ከተማው የህብረተሰቡን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን መንግስት የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ከነዚህም አንዱ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ በወረዳዎች እውን በማድረግ የህብረተሰባችንን የአገልግሎት ፍላጎት እናረጋግጣለን ብለዋል።