በክፍለ ከተማው የ2017 ትምህርት ዘመን የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በስኬት ለማጠናቀቅ የባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ መሆኑን ተገለጸ።

user 05-Jun-2025 ልማት

በክፍለ ከተማው የ2017 ትምህርት ዘመን የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በስኬት ለማጠናቀቅ የባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ መሆኑን ተገለጸ።

‎(ጉለሌ ኮሙኒኬሽን ፣ 27 -09 -2017 ዓ.ም)

‎የጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በሰላም ለማጠናቀቅ ከፈተና ኮማንድ ፖስት ፣ ከትምህርት ዘርፉ አመራሮች ፣ ሱፐርቫይዘሮች ፣ ለመምህራን ፣ ለጸጥታ አካላትና ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት ኦረንቴሽን ሰጥቷል።

‎በክፍለ ከተማው ሰኔ 2/2017 ዓ.ም ጀምሮ በክፍለ /ከተማው ባሉ በሚገኙ የፈተና ጣቢያዎች ከተማ አቀፍ የ6ኛና 8ኛ ክፍል ፈተና እንደሚሰጥ ተገልጿል ።

‎የጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ እንደተናገሩት ፈተናው ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ በትኩረት መስራት ይገባል ብለው ተማሪዎች ውጤታማ የማጠቃለያ ፈተና እንዲያደርጉ ሁሉም ባላድርሻ አካላት የቅድመ ዝግጅት ስራቸውን እንዲያጠናቁ ያሉ ሲሆን በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥም ሆነ ከውጭ ሊከናወኑ የሚችሉ የፈተና ግድፈቶችን ከበፊት ከነበረን የስራ አፈጻጸም ተነስተን ችግሮች እንዳይፈጠሩ መስራት ይገባል ብለዋል።

Related Post

ልዩ ዜና