በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ወረዳዎች የሺኖዬ እና ጎቤ ባህላዊ እሴቱንና ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ በደማቅ ባህላዊ ክዋኔዎች ተከበረ ፡፡

user 07-Sep-2025 መዝናኛ

በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ወረዳዎች የሺኖዬ እና ጎቤ ባህላዊ እሴቱንና ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ በደማቅ ባህላዊ ክዋኔዎች ተከበረ ፡፡

በዓሉ በኦሮሞ ባህል የዘመን መለወጫ ማብሰርያ የሆነውንና የዝናብ ወቅት ማለቁን የፀደይ ጊዜ መምጣቱን ለመግለጽ በኦሮሞ ወጣቶች የሚከበረው የሺኖዬ እና ጎቤ በደማቅ ባህላዊ ጨዋታ ክዋኔዎች በተለያዩ ወረዳዎች ተከብሯል፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የስራ ክህሎት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሰሎሞን ታደሰ በወረዳዎች ተዘዋውረው ምልከታ አድርገዋል።

ሀላፊው በበአሉ መልዕክት እንዳስተላለፉት የጎቤ እና ሺኖዬ በዓል እድሜያቸው ከአስራዎቹ መጀመሪያ እስከ ሃያዎቹ አጋማሽ ድረስ ያሉ ልጃገረዶችና እና ወጣት ወንዶች ተሰባስበው የሚያከብሩት ባህላዊ ጨዋታ ሲሆን ወጣቶች ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ የመረዳዳት ፣መደጋገፍና አብሮነትን በማጠናከር ወጣቱ በየትኛውም ሀገራዊ ልማት በመሳተፍ ኢትዮጵያዊ እሴቶችን አጠናክሮ ማክበር ከሁሉም የሚጠበቅ ሀላፊነት መሆኑን ተናግረዋል።

Related Post

ልዩ ዜና